Alkeso Mosque
የወራቤ ከተማ ምስል - ገፅታ
Worabe hospital
Worabe hospital
Worabe poly collage
Worabe poly collage
worabemuzym
Worabe muzym
Alkeso Mosque
አልከሶ መስጊድ - ታሪካዊ ቅርስ
Alkeso Mosque Interior
የአልከሶ መስጊድ የውስጣዊ ክፍል - ታሪካዊ ቅርስ
Kitab
ኪታብ - ታሪካዊ ቅርስ
Deresa
የአልከሶ ደረሳሶ - ታሪካዊ ቅርስ
Zepho Waterfall
ዘፎ ፏፏቴ - ተፈጥሯዊ ውበት
Gunda Bridge
ጉንዳ ተፈጥሯዊ ድልድይ
Werabe City
ወራቤ ከተማ - የስልጤ ዞን መቀመጫ
Genbo Cave
ገንቦ ዋሻ - ጥንታዊ ቅርስ
Gudro Forest
የጉድሮ ደን
Siltie Culture
የስልጤ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች - ጥንታዊ ቅርስ
Genbo Cave 2
ገንቦ ዋሻ - ጥንታዊ ቅርስ

ወራቤ ከተማ ስታቲስቲካል አስትራክት

2012-2017 ዓ.ም ሙሉ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መረጃ

ሁሉም ክፍሎች ይታያሉ

1. የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፕላን ጽ/ቤት

ራዕይ

ወራቤ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ፣ ተደራሽ አገልግሎት ያላት፣ ኢንቨስትመንት የሚስብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የኑሮ ሁኔታ ያላት ከተማ ለመሆን።

ተልዕኮ

የከተማውን ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ተመጣጣኝ መረጃ በመሰብሰብ፣ በመተንተን እና በማሰራጨት ለእቅድ አውጪዎች፣ ለወሳኝ አካላት እና ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት።

እሴቶች
  • ግልጽነት እና ተጠያቂነት
  • የመረጃ ጥራት እና ትክክለኛነት
  • የህብረተሰብ ተሳትፎ
  • ቀጣይነት ያለው ልማት
  • ፍትሃዊነት እና እኩልነት

3. መልእክቶች

Mayor of Werabe City
የከተማው ከንቲባ
የወራቤ ከተማ አስተዳደር

ያሲን ከሊል

የከንቲባው መልእክት

ለወራቤ ከተማ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች ሁሉ እንኳን ደህና መጣቹ።

ወራቤ ከተማ በስልጤ ዞን ውስጥ ፈጣን እድገት እያሳየች ያለች ከተማ ናት። በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመሰረተ ልማት፣ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች የልማት ዘርፎች ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበች ትገኛለች።

ይህ ድረ-ገጽ የከተማችንን አጠቃላይ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መረጃ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ የተዘጋጀ ነው። እያንዳንዱ ዜጋ የከተማውን እድገት በመከታተል ለልማቱ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ እናቀርባለን።

በመተባበር ወራቤን ለሁላችን ምቹ ከተማ እንገንባ!

የወራቤ ከተማ ከንቲባ

Plan and Development Office Head
የፕላን እና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
የወራቤ ከተማ አስተዳደር
የፕላን እና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ መልእክት

ለወራቤ ከተማ ነዋሪዎች እንኳን ደህና መጣቹ።

የፕላን እና ልማት ጽ/ቤታችን የከተማውን ልማት ለማራመድ የሚያስችሉ እቅዶችን በማውጣት እና በመተግበር ላይ ይገኛል። በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ እቅድ ለዘላቂ ልማት መሰረት ነው።

ይህ ድረ-ገጽ የከተማችንን ስታቲስቲካል መረጃ ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ለውሳኔ ሰጪዎች፣ ለባለሃብቶች እና ለህብረተሰቡ ጠቃሚ መረጃ ይዟል።

ለከተማችን እድገት ሁላችንም አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን።

ሳዲቅ ስርጋጋ

የፕላን እና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ

2. የከተማው ታሪካዊ አመሰራረት

ከ1958 ዓ.ም በፊት ወራቤ ትንሽ መንደርና የገጠር ከተማ የነበረች ሲሆን ምንም ዓይነት ማህበራዊ ተቋማት ያልነበሯትና በመንደሯም ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ቁጥር በጣም ጥቂት እንደነበር የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ። በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪ ለትምህርት፣ ለጤናና አስተዳደራዊ ነክ ጉዳዮች ቡታጅራና ዝዋይ ከተሞች ይመላለስ እንደነበር ማወቅ ይቻላል። ሆኖም በ1958 ዓ.ም ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ወራቤን የመጎብኘት እድል ገጥሟቸው ነበር።

ወራቤ የስልጤ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው፡- ሚያዚያ 23 ቀን 1993 ዓ.ም በተደረገው የስልጤ ብሔረሰብ የማንነት ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ ነው። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በከተማ አስተዳደርነት ደረጃ መተዳደር ከጀመረች ጊዜ ጀምሮ በፈጣን እድገት ውስጥ ከሚገኙ የአገራችን ከተሞች አንዷ ሆናለች።

ቁልፍ ነጥብ፡ ወራቤ ከአዲስ አበባ 172 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በአዲስ አበባ-ሆሳዕና ዋና መንገድ ላይ ትገኛለች።

2. የከተማው ጂኦግራፊያዊ ሁኔታ እና የቀበሌዎች ካርታ

ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ

የወራቤ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ 172 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ እስከ ጅንካ የተዘረጋው አስፋልት አቋርጧት የሚያልፍ መሆኑ ለከተማዋ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በሰሜን ቅቤት፣ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ሁልባረግ፣ በምስራቅ ዳሎቻ፣ በምዕራብ አሊቾ ውሪሮ ጋር ትዋሰናለች።

የቆዳ ስፋትና አስተዳደራዊ አወቃቀር
Werabe City Administrative Map

ምስል 1፡ የወራቤ ከተማ አስተዳደራዊ ካርታ

17,800 ሄክታር
አጠቃላይ የቆዳ ስፋት
11
ቀበሌዎች (3 ከተማ + 8 ገጠር)
መልከዓምድራዊ ገጽታና የአየር ጸባይ

የወራቤ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ 8° ላቲቲዩድ እና 38° ሎንግቲዩድ ከባህር ጠለል በላይ ከ2080-2100 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አብዛኛው ሜዳማ መልክዓ-ምድራዊ ገጽታ ሲኖረው የተቀረው ተራራማና ገደላገደል ገጽታ አለው። ከተማዋን የሚያቋርጡ ዲጆና ልማዛ ወንዞች ይገኙባታል። የዝናብ መጠኗም እስከ 1200 ሚ.ሜ ሲሆን የሙቀት መጠንዋ ከፍተኛው 22°C ዝቅተኛው 15°C ነው። የአየር ጸባይዋም ወይና ደጋ የአየር ጸባይ ካላቸው ይመደባል።

2080-2100 ሜ
ከባህር ጠለል በላይ
15-22°C
አማካይ የሙቀት መጠን
1200 ሚ.ሜ
አማካይ ዓመታዊ ዝናብ

የአየር ጸባይ፡ ወይና ደጋ | ዋና ወንዞች፡ ዲጆ፣ ልማዛ፣ ዘይወቴ

የቀበሌዎች ካርታ

ከዚህ በታች የወራቤ ከተማ 10 ቀበሌዎች ካርታዎች ቀርበዋል። እያንዳንዱ ካርታ የቀበሌውን ድንበር እና አቀማመጥ ያሳያል።

Werabe Town 01+02 Map
ወራቤ ከተማ 01+02
Alkeso Town Map
አልከሶ ከተማ
Anshobeso Map
አንሻቤሶ
Agedele Anshobeso Map
አገደሌ አንሻቤሶ
Diledate Map
ድሌ ዳጤ
Buraqa Map
ቡርቃ
Germama Map
ገርማማ
Date Wezir 6 Map
ዳጤ ወዚር 6
Fugie Acherae Map
ፉጌ አጭራዬ
Albazer Map
አልባዘር
ማስታወሻ፡ ካርታዎቹ ለማሳያ ዓላማ ቀርበዋል። የቀበሌዎቹ ድንበሮች እንደየመረጃ ምንጭ ሊለያዩ ይችላሉ።

4. የህዝብ ብዛት ስብጥርና አሰፋፈር

የከተማዋ ነዋሪ ብዛት ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል፡፡ በ2012 ዓ.ም 84,512 የነበረው ህዝብ ብዛት በ2013 ዓ.ም 87,574፣ በ2014 ዓ.ም 91,602፣ በ2015 ዓ.ም 97,276፣ በ2016 ዓ.ም 101,945 እና በ2017 ዓ.ም 106,839 ደርሷል፡፡ በ2017 ዓ.ም ከጠቅላላው ህዝብ ብዛት ውስጥ ወንድ 51,865 እና ሴት 54,974 ናቸው፡፡ በከተማዋ የተለያዮ ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የስልጤ፣ የሀድያና የጉራጌ ብሄረሰቦች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ስልጥኛና አማርኛ በከተማው በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ሲሆኑ ስልጥኛ እና አማርኛ የስራ ቋንቋ ናቸዉ፡፡ በአምስት ዓመታት ውስጥ የህዝብ ብዛት በ22,327 (26.4%) አድጓል፡፡

የህዝብ ብዛት እድገት (2012-2017) / Population Growth
የህዝብ ብዛት በፆታ (2017) / Population by Sex
የህዝብ ብዛት በቀበሌ (2017) / Population by Kebele
የህዝብ ብዛት በቀበሌ፣ በፆታ እና በዓመት (2012-2017 ዓ.ም)

POPULATION SIZE BY SEX, KEBELE AND YEAR BASED ON 1999 CSA CENSUS DATA - WORABE TOWN ADMINISTRATION 2012-2017 E.C

2012 E.C - Total: 84,512
YEAR S.NO NAME OF KEBELE MALE FEMALE TOTAL
2012 1 WERABE TOWN 01+02 14,105 13,772 27,877
20122ALKESO TOWN9108991,809
20123ARAT BER5,3265,63910,965
20124ANSHOBESO5,6245,96411,588
20125AGEDELE ANSHOBESO1,0481,0802,128
20126DILEDATE7127561,468
20127GERMAMA GALE2,7092,8455,554
20128DATE WEZIR 64,2194,5378,756
20129FUGIE ACHERAE4,3974,8959,292
2012 10 ALBAZER 2,410 2,666 5,076
2012 TOTAL 41,459 43,053 84,512
YEAR S.NO NAME OF KEBELE MALE FEMALE TOTAL
20131WERABE TOWN 01+0215,40015,03630,436
20132ALKESO TOWN1,1101,1012,211
20133ANSHOBESO9,67110,25619,928
20134AGEDELE ANSHOBESO1,1441,1792,323
20135DILEDATE7778251,603
20136BURAQA8528751,726
20137GERMAMA2,0622,0374,100
20138DATE WEZER 64,6064,9549,560
20139FUGIE ACHERAE4,8015,34410,145
201310ALBAZER2,6312,9115,542
2013TOTAL43,05544,51987,574
YEAR S.NO NAME OF KEBELE MALE FEMALE TOTAL
20141WERABE TOWN 01+0216,10815,72831,836
20142ALKESO TOWN1,1611,1522,313
20143ANSHOBESO10,11610,72820,844
20144AGEDELE ANSHOBESO1,1971,2332,430
20145DILEDATE8138631,676
20146BURAQA8919151,806
20147GERMAMA2,1572,1314,288
20148DATE WEZER 64,8185,18110,000
20149FUGIE ACHERAE5,0215,59010,612
201410ALBAZER2,7523,0455,797
2014TOTAL45,03546,56791,602
YEAR S.NO NAME OF KEBELE MALE FEMALE TOTAL
20151WERABE TOWN 01+0216,94716,55233,500
20152ALKESO TOWN1,2811,2702,551
20153ANSHOBESO10,66611,30621,972
20154AGEDELE ANSHOBESO1,3181,3552,674
20155DILEDATE9169681,884
20156BURAQA9971,0222,019
20157GERMAMA2,3252,2964,621
20158DATE WEZER 65,1135,49310,606
20159FUGIE ACHERAE5,3265,92111,248
201510ALBAZER2,9483,2546,202
2015TOTAL47,83849,43797,276
YEAR S.NO NAME OF KEBELE MALE FEMALE TOTAL
20161WERABE TOWN 01+0217,76017,34635,408
20162ALKESO TOWN1,3421,3302,673
20163ANSHOBESO11,17711,84823,026
20164AGEDELE ANSHOBESO1,3181,4202,802
20165DILEDATE9601,0141,974
20166BURAQA9971,0712,114
20167GERMAMA2,3252,4064,842
20168DATE WEZER 65,3585,75611,115
20169FUGIE ACHERAE5,5816,20511,787
201610ALBAZER3,0893,4106,499
2016TOTAL50,01151,934101,945
YEAR S.NO NAME OF KEBELE MALE FEMALE TOTAL
20171WERABE TOWN 01+0218,56919,47838,047
20172ALKESO TOWN1,3361,3262,662
20173ANSHOBESO11,64412,34823,992
20174AGEDELE ANSHOBESO1,3781,4202,797
20175DILEDATE9369941,930
20176BURAQA1,0251,0532,078
20177GERMAMA2,4832,4534,936
20178DATE WEZER 65,5465,96411,510
20179FUGIE ACHERAE5,7806,43412,214
201710ALBAZER3,1683,5046,672
2017TOTAL51,86554,975106,839
ማጠቃለያ ትንተና / Summary Analysis
  • አጠቃላይ የህዝብ ብዛት እድገት፡- ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የከተማዋ ህዝብ ብዛት ከ84,512 ወደ 106,839 አድጓል።
  • አጠቃላይ የእድገት መጠን፡- በአምስት ዓመታት ውስጥ 22,327 (26.4%) የህዝብ ብዛት ጭማሪ ተመዝግቧል።
  • አማካይ ዓመታዊ የእድገት መጠን፡- በየዓመቱ በአማካይ 4.8% የህዝብ ብዛት ጭማሪ አሳይቷል።
  • የፆታ ስርጭት፡- በሁሉም ዓመታት የሴቶች ብዛት ከወንዶች ይበልጣል።
  • ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላቸው ቀበሌዎች፡- ወራቤ ከተማ 01 እና 02፣ አንሻቤሶ እና ፉጌ አጭራዬ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት አላቸው።
  • ዝቅተኛ የህዝብ ብዛት ያላቸው ቀበሌዎች፡- ድሌ ዳጤ፣ ቡርቃ እና አልከሶ ከተማ ዝቅተኛ የህዝብ ብዛት አላቸው።
ዓመት / Year ወንድ / Male ሴት / Female ድምር / Total የእድገት መጠን / Growth Rate
201241,45943,05384,512-
201343,05544,51987,574+3.6%
201445,03546,56791,602+4.6%
201547,83849,43797,276+6.2%
201650,01151,934101,945+4.8%
201751,86554,975106,839+4.8%
አጠቃላይ ጭማሪ+10,406+11,922+22,327+26.4%

ምንጭ፡- በ1999 ዓ.ም የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ (ሲኤስኤ) ቆጠራ መረጃ መሰረት

5. የተፈጥሮ ሀብት

የወራቤ ከተማ በብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች የተባረከች ናት። ዋና ዋናዎቹ፡-

💧 የውሃ ሀብት

ዲጆ፣ ልማዛ እና ዘይወቴ ወንዞች ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ እና ለቤተሰብ አገልግሎት ያገለግላሉ።

⛏️ የግንባታ ዕቃዎች

ነጭ ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ጭቃ እና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶች በስፋት ይገኛሉ።

⛰️ ተራሮች

ጋፋት እና ዳጤ ወዚር 6 ተራሮች ለቱሪዝም እና ለከብት እርባታ ተስማሚ ናቸው።

6. ማህበራዊ ሁኔታ

ትምህርት

ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገትና ልማት ቁልፍ መሣሪያ ነው። በወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ስር ከ2014-2017 ዓ/ም ድረስ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ት/ት ቤቶች እንደሚከተለው ናቸው።

የትምህርት ቤቶች እድገት / School Growth
የተማሪዎች ስርጭት በፆታ (2017) / Student Distribution by Sex
የመንግስት እና የግል ት/ት ቤቶች ብዛት (2014-2017 ዓ.ም)
ዓ/ም የመንግስት ት/ት ቤት ብዛት የግል ት/ት ቤት ብዛት ቅድመ አንደኛ ብዛት የጎልማሳ ጣቢያ ብዛት
20142185547
20152195648
201621105949
201722126150
በመንግስት ት/ት ቤት የሴክሽን ብዛት በክፍል ደረጃ (1-8)
የክፍል ደረጃ1ኛ2ኛ3ኛ4ኛ5ኛ6ኛ7ኛ8ኛ1ኛ-8ኛ
የሴክሽን ብዛት3835353233313030264
በመንግስት ት/ት ቤት የሴክሽን ብዛት በክፍል ደረጃ (9-12)
የክፍል ደረጃ9ኛ10ኛ11ኛ12ኛ9ኛ-12ኛ
የሴክሽን ብዛት251110955
በግል ት/ት ቤት የሴክሽን ብዛት በክፍል ደረጃ
ተ.ቁየክፍል ደረጃየሴክሽን ብዛት
11ኛ ክፍል22
22ኛ ክፍል17
33ኛ ክፍል15
44ኛ ክፍል11
55ኛ ክፍል10
66ኛ ክፍል7
77ኛ ክፍል7
88ኛ ክፍል5
1ኛ ክፍል - 8ኛ ክፍል94
ተ.ቁየክፍል ደረጃየሴክሽን ብዛት
19ኛ ክፍል5
210ኛ ክፍል4
311ኛ ክፍል3
412ኛ ክፍል3
9ኛ ክፍል - 12ኛ ክፍል15
2017 በዓመቱ ለመማር የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት መረጃ (መንግስት ት/ት ቤት)
የክፍል ደረጃወንድሴትድምር
1ኛ ክፍል1,2001,2432,443
2ኛ ክፍል1,0751,0082,083
3ኛ ክፍል1,0721,0602,132
4ኛ ክፍል9889551,943
5ኛ ክፍል8488371,685
6ኛ ክፍል8418241,665
7ኛ ክፍል7657811,546
8ኛ ክፍል8228861,708
9ኛ ክፍል7489611,709
10ኛ ክፍል290373663
11ኛ ክፍል295449744
12ኛ ክፍል261373634
ጠቅላላ9,2059,75018,955
2017 በማታው የት/ት ፕሮግራም የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት
የክፍል ደረጃወንድሴትድምር
1ኛ ክፍል426
2ኛ ክፍል8917
3ኛ ክፍል121022
4ኛ ክፍል162238
5ኛ ክፍል181230
6ኛ ክፍል12921
7ኛ ክፍል151025
8ኛ ክፍል151126
ጠቅላላ10085185
2017 በግል ት/ት ቤት የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት
የክፍል ደረጃወንድሴትድምር
1ኛ ክፍል406411817
2ኛ ክፍል283279562
3ኛ ክፍል209240449
4ኛ ክፍል195161356
5ኛ ክፍል126151277
6ኛ ክፍል131133264
7ኛ ክፍል8696182
8ኛ ክፍል6271133
9ኛ ክፍል8832120
10ኛ ክፍል8040120
11ኛ ክፍል8729116
12ኛ ክፍል8325108
ጠቅላላ1,8361,6683,504
ጥምርታዎች
1:62
የተማሪ-ክፍል ጥምርታ (1-8)
1:62
የተማሪ-መምህር ጥምርታ (1-8)
1:5
የተማሪ-መጽሃፍ ጥምርታ (1-6)
1:6
የተማሪ-መጽሃፍ ጥምርታ (7-8)
1:59
የተማሪ-ክፍል ጥምርታ (9-12)
1:2
የተማሪ-መጽሃፍ ጥምርታ (9-12)
በአጠቃላይ በወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ስር ከ2014-2017 ዓ/ም ድረስ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ት/ት ቤቶች ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ይገኛሉ።
ጤና

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራቸው ካሉ ስራዎች አንዱ የጤና ልማት ስራ ነው። ከተማ አስተዳደሩ ሲመሰረት አንድ የማህበረሰብ ክሊኒክ የነበረ ሲሆን እያደገ የመጣውን የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት መነሻ በማድረግ የጤና ተቋማት ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል።

የጤና ተቋማት እድገት / Health Facilities Growth
የጤና ባለሙያዎች ስርጭት / Health Professionals Distribution
የጤና ተቋማት መረጃ (2015-2017 ዓ.ም)
የተቋም አይነት እስከ 2015 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም
ጤና ጣቢያ23 (አዲስ በመገንባት ላይ)
ጤና ኬላ1010
ኮምፐርሀንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል11
የግል መካከለኛ ክሊኒክ821 (+13 አዲስ)
የግል መድሀኒት መደብር1014 (+4 አዲስ)
የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ሽፋን፡ 80%
የዲግሪ ባለሙያዎች ብዛት (2017 ዓ.ም)
ተ.ቁየሙያ መስክወንድሴትድምር
1የጤና መኮንን111425
2ዶክተር202
3ኢንቫይሮሜንተል ሄልዝ ፕሮፌሽናል303
4ነርስ ዲግሪ213
5ሚድ ዋይፍ ነርስ ፕሮፌሽናል101
6ፋርማሲስት112
7ላቦራቶሪ ቴክኖሎጅስት022
ጠቅላላ201838
የዲፕሎማ ባለሙያዎች ብዛት (2017 ዓ.ም)
ተ.ቁየሙያ መስክወንድሴትድምር
1ክሊኒካል ነርስ42933
2ፐብሊክ ነርስ044
3ሚድ ዋይፍ ነርስ01818
4ድራጊስት1910
5ላቦራቶሪ ቴክኒሸን4610
6ሳኒቴሪያን134
ጠቅላላ106979
የላቦራቶሪ እና መድሀኒት ቤቶች መረጃ
የመንግስት ተቋምብዛት
ላቦራቶሪ2
መድሀኒት መደብር2
የግል ድርጅትብዛት
መድሀኒት መደብር12
ፋርማሲ1
የጤና አገልግሎት መረጃ (2017 ዓ.ም)
171,157
ተመላላሽ ታካሚ
174,957
አጠቃላይ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚዎች
8,958,745 ብር
አመታዊ ገቢ
98%
የአካባቢ ንጽህና ሽፋን
የእናቶች ጤና አገልግሎት መረጃ
የወሊድ አገልግሎት ያገኙ እናቶች ብዛት3,251
የወሊድ መከላከያ የተጠቀሙ ሴቶች ብዛት19,988
የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ቢያንስ አንድ ጊዜ ያገኙ እናቶች3,390
የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ቢያንስ አራት ጊዜ ያገኙ እናቶች2,922
የድህረ ወሊድ አገልግሎት (ከ2-7 ቀናት) ያገኙ3,122
የአንዲት እናት አጠቃላይ የወልደት መጠን4.9
የወሊድ አገልግሎት ሽፋን80%
የህጻናት ጤና እና አልምነት መረጃ
922
ከአምስት አመት በታች ክብደት የቀነሱ ህጻናት
229
የመቀንጨር ችግር ያለባቸው ህጻናት
0
የጨቅላ ህጻናት መጠነ ሞት (ከ1000)
የክትባት አገልግሎት መረጃ
የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ያገኙ ህጻናት4,838
የሳምባ ምች መከላከያ ክትባት (ፒ.ሲ.ቪ 3ኛ ጊዜ)3,053
ሁሉንም ክትባት የተሟላ ወሰዱ ህጻናት4,768
የአልጋ አጎበር ተጠቃሚዎች ብዛት (2017)፡ 69,064
የኤች አይ ቪ መከላከል አገልግሎት መረጃ (2017)
ኤች አይ ቪ ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤታቸውን ያወቁ ሰዎች4,688
ኤች አይ ቪ ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤታቸውን ያወቁ እናቶች3,390
ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ክትትል የሚደረግላቸው እናቶች3
ኤች አይ ቪ መድሀኒት እየወሰዱ ያሉ ሰዎች230
ኤች አይ ቪ መድሀኒት እየወሰዱ ያሉ እናቶች128
አዲስ ህክምና የጀመሩ ሰዎች5
የአካል ጉዳተኞች ብዛት በአይነት
የአካል ጉዳቱ አይነትብዛት
ማየት የተሳናቸው23
የእጅ ጉዳት18
የእግር ጉዳት85
የአምሮ ውስንነት30
ጠቅላላ156
ዋና ዋና ስኬቶች፡
  • የእናቶች ሞት በ2015-2017 ምንም አልተመዘገበም
  • ህጻናት ሞት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል
  • ኤች አይ ቪ ኤድስ እና ወባ ስርጭት ቀንሷል
  • የአካባቢ ንጽህና ሽፋን 98% ላይ ደርሷል
ቱሪዝም

ወራቤ ብዙ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች አሏት፡

Alkeso Mosque
አልከሶ መስጊድ

አልከሶ መስጊድ በወራቤ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት የቱሪስት መስህብ ቦታዎች አንድ እና ዋነኛው ሲሆን ከማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ውስጥ ይመደባል፡፡ አልከስዬ እ.ኢ.አ 1858 ዓ.ም እንዶፎ በሚባል ደጋማ አከባቢ ተወለዱ፡፡ እ.ኢ.አ 1935 በ77 አመታቸው የአልከሶን መስጊድ ለመገንባት ሲያስቡ 360 በላይ የጽድ ፍልጦችን አምጥተዋል።

Zepho Waterfall
ዘፎ ፏፏቴ

33 ሜትር ቁመት ያለው ተፈጥሯዊ ፏፏቴ ሲሆን ከማይንቀሳቀስ ቅርስ ይመደባል፡፡ ፏፏቴው ወርዶ የሚያርፍበት ትንሽ ወንዝ ጥልቀቱ 12 ሜትር በላይ እንደሆነ ይገመታል። የከተማው ነዋሪዎች ለመዋኘትና ፎቶ ግራፍ ለመስራት ይመጣሉ።

Genbo Cave
ገንቦ ዋሻ

በወራቤ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኘው የገንቦ ዋሻ በገሜ ጎጥ በዘይወት ወንዝ በስተ ምስራቅ ይገኛል። አንድ ትልቅ መግቢያ ያለው ሲሆን ወደ ውስጥ ሲገባ በሁለት የተከፈሉ መንገዶች አሉት። ሁለት መግቢያ ያለው ተፈጥሯዊ ዋሻ ነው።

Gunda Natural Bridge
ጉንዳ ተፈጥሯዊ ድልድይ

የጉንዳ ድልድይ ከተፈጥሮ የመስህብ ቦታዎች ሲመደብ ከማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ ነው። በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ ከዋናው መንገድ 22 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። የተፈጥሮአዊ ድልድይ ስፋቱ 1 ሜትር ሲሆን የክብ ቀዳዳው ስፋት 3 ሜትር ነው። ጥልቀቱ 7 ሜትር ያህል ነው።

Gudro Forest
የጉድሮ ደን

የጉድሮ ተፈጥሯዊ ደን በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ በዳጤ ወዘር 6 ቀበሌ ከከተማው ከዋናው መንገድ በስተሰሜን 11 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። በደኑ ውስጥ ጅብ፣ ቀበሮ፣ ሚዳቆ፣ ጥንቸል፣ ዠግራ እና ቆቅ ይገኛሉ።

Siltie Cultural Artifacts
የስልጤ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች

የስልጤ ብሔረሰብ የበለጸገ ባህላዊ ቅርስ አለው። የተለያዩ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች በወራቤ ከተማ ይገኛሉ። እነዚህ ቅርሶች የስልጤ ህዝብ ባህላዊ ማንነት የሚያንጸባርቁ ናቸው።

7. የከተማ ግብርና

ግብርና በከተማው ውስጥ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የእንሰሳት ሀብት / Livestock Population
የአርሶ አደሮች መረጃ (2017 ዓ.ም)
36
ወንድ አርሶ አደሮች
13
ሴት አርሶ አደሮች
49
ጠቅላላ
ሰብል ልማት

በከተማው ውስጥ የሚመረቱ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ጤፍ፣ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ናቸው። በ2017 ዓ.ም ዋና ዋና ሰብሎች ምርታማነት፡ በቆሎ 49 ኩ/ሄ፣ ስንዴ 42 ኩ/ሄ፣ ጤፍ 18 ኩ/ሄ።

የእንሰሳት ሀብት
86,744
ከብት
98,770
ፍየል
28,239
በግ
225,424
ዶሮ
8,802
አህያ
2,353
ፈረስ

8. የመሰረተ ልማት አቅርቦት

መሰረተ ልማት ለከተማው እድገት ወሳኝ ነው። በ2017 ዓ.ም የተሟሉ ዋና ዋና አቅርቦቶች፡

መንገዶች
  • አስፋልት፡ 16 ኪ.ሜ
  • ጠጠር፡ 39.9 ኪ.ሜ
  • ኮብል ስቶን በኮሪደር ልማት
ኤሌክትሪክ

24 ሰዓት የውሃ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ

ውሃ

የውሃ መስመር ዝርጋታ፡ 9.4 ኪ.ሜ | የጎርፍ መውረጃ ቦይ፡ 19

ቴሌኮም

ዲጂታል ስልክ፣ 4ጂ፣ ኢንተርኔት አገልግሎት ይሰጣል።

9. ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት

በከተማው ውስጥ ስራ ፈላጊዎችን በማህበር በማደራጀት፣ ብድር በማመቻቸትና ቦታ በመስጠት የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።

የተፈጠረ የስራ እድል (2015-2017) / Jobs Created
የተፈጠረ የስራ እድል (2015-2017 ዓ.ም)
ዓመትወንድሴትድምር
20152,1239183,041
20162,2701,0723,342
20173,7481,9675,715
ጠቅላላ8,1413,95712,098

10. የህብረት ስራ የመኖሪያ ማህበራት

የህብረት ስራ የመኖሪያ ማህበራት መረጃ

በወራቤ ከተማ በ2008-2015 ዓ.ም የተመዘገቡ የህብረት ስራ የመኖሪያ ማህበራት መረጃ ከዚህ በታች ቀርቧል። በአጠቃላይ 133 ማህበራት ተመዝግበዋል።

የተላለፈበት ዓመት የማህበር ብዛት
20086
200912
201021
201111
201214
201325
201428
201541
ድምር133
የማህበራት ብዛት እድገት (2008-2015)
ከ2008 እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ በወራቤ ከተማ 133 የህብረት ስራ የመኖሪያ ማህበራት ተመዝግበዋል። ከፍተኛው እድገት በ2015 ዓ.ም ተመዝግቧል።
በህብረትስ ስራ መኖሪያ ማህበራት ተጠቃሚዎች መረጃ

ከ2008-2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ በህብረት ስራ መኖሪያ ማህበራት የተጠቀሙ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች አካላት እንዲሁም የተፈጠረው የስራ እድል እና የተሰጠው የመሬት መጠን ከዚህ በታች ቀርቧል።

የተላለፈበት ዓመት (2008-2015) የማህበር ብዛት ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚ አካላት የተፈጠረ ስራ ዕድል የመሬት መጠን (ሄክታር)
2008-2015 133 4207901,210 1,1067901,896 1,9452,2584,203 --
ጠቅላላ / Total 4207901,210 1,1067901,896 1,9452,2584,203 --
ተጠቃሚዎች እና የተፈጠረ ስራ
የመሬት አጠቃቀም ስርጭት
በአጠቃላይ 1,210 ወጣቶች እና ሴቶች፣ 1,896 አካላት ተጠቃሚ ሲሆኑ 4,203 የስራ እድሎች ተፈጥረዋል።
የቤት መረጃ

ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ በህብረት ስራ መኖሪያ ማህበራት የተገነቡ የቤቶች ብዛት ከዚህ በታች ቀርቧል።

ዓመት ብዛት
201121
201221
201328
201433
20152
ድምር105
የቤቶች ብዛት እድገት (2011-2015)
ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ በህብረት ስራ መኖሪያ ማህበራት በኩል በድምሩ 105 ቤቶች ተገንብተዋል። ከፍተኛው ግንባታ በ2014 ዓ.ም (33 ቤቶች) ተመዝግቧል።

10. ፋይናንስ

የገቢ መረጃ ትንተና (2012-2018 ክንውን)

የወራቤ ከተማ አጠቃላይ ገቢ፣ መደበኛ ገቢ እና የማዘጋጃ ቤት ገቢ ከ2012 እስከ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።

ምድብ 2012 ክንውን 2013 ክንውን 2014 ክንውን 2015 ክንውን 2016 ክንውን 2017 ክንውን 2018 ክንውን
ጠቅላለ ገቢ ብር 95,534,204 130,723,596 198,519,059 274,574,455 346,020,649 536,679,021 1,071,526,166
መደበኛ ገቢ ብር 50,341,352 73,838,124 119,869,599 175,439,699 213,708,965 324,277,053 734,691,515
ማዘጋጃ ቤት ገቢ ብር 45,192,852 56,885,471 78,649,459 99,134,756 132,311,684 212,401,968 336,834,651
የወራቤ ከተማ የገቢ እድገት (2012-2018) / Income Growth
ዋና ምልከታዎች፡
  • በሁሉም ምድቦች ውስጥ ጉልህ የሆነ የገቢ እድገት አለ።
  • በተለይ 2017 እና 2018 መካከል በጣም ከፍተኛ እድገት ታይቷል።

የወራቤ ከተማ አጠቃላይ የፋይናንስ ሀብት በለፉት አምስት ዓመታት በአማካይ 69.7% እያደገ የመጣ ሲሆን፣ ከ255 ሚሊዮን ብር (2014) ወደ 842 ሚሊዮን ብር (2018 እቅድ) አድጓል።

መደበኛ ወጪ አፈጻጸም / Regular Expenditure (2011-2015)
የትሬዠሪ/የመንግስት ድጎማ / Treasury Subsidy (2011-2015)
የካፒታል በጀት ወጪ / Capital Budget Expenditure (2011-2015)
መደበኛ ወጪ አፈጻጸም (2011-2015) በብር
ዓመት መደበኛ ወጪ
2011111,941,464
2012136,814,991
2013188,887,100.42
2014264,391,895.12
2015344,404,693.67
የትሬዠሪ/የመንግስት ድጎማ በጀት (2011-2015)
ዓመትየትሬዠሪ ድጎማ (ብር)
201136,549,789
201236,723,060
201350,142,978
201460,185,758
201563,261,281
የካፒታል በጀት ወጪ (2011-2015)
ዓመትየካፒታል ወጪ (ብር)
201135,007,271
201240,556,292.19
201337,479,592
201451,862,544.9
2015107,681,181

12. የመሬት አጠቃቀም መረጃ

የተያዘላት ዘርፍ አፈጻጸም
የተያዘላት ዘርፍ የታቀደ መጠን (ሄክታር) አፈጻጸም መጠን (ሄክታር) መቶኛ (%)
መኖሪያ1,887.96308.0216.61%
አስተዳደር314.6638.582.08%
ንግድ እና ተጓዳኝ629.328137.9447.44%
ማምረቻ እና ማከማቻ692.252127.776.89%
ማህበራዊ እና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶች1,321.572287.26215.49%
ትራንስፖርት1,887.96488.1126.33%
መዝናኛ እና ያልለሙ አካባቢዎች3,108.79539.702.14%
ጠቅላላ15,733.001,853.919100%

በማውቅራዊ ፕላን የተካተተው የሰፈር ልማት ትግበራ ከግማሽ በላይ የሚሆነው መልማቱን የሰያል። በዕቅድ ከተያዘው የመሬት አጠቃቀም ለመኖሪያ 1887.96 ሄ/ር ውስጥ 308.02 ሄ/ር (16.61%)፣ ለአስተዳደር ከ314.66ሄ/ር ውስጥ 38.58ሄ/ር (2.08%)፣ ለንግድ እና ተጓዳኝ ከ629.328 ሄ/ር ውስጥ 137.944 ሄ/ር (7.44%)፣ ከማምረቻና ማከማቻ ከ692.252 ሄ/ር ውስጥ 127.77 ሄ/ር (6.89%)፣ ከማህበራዊና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶች ከ1321.572 ሄ/ር ውስጥ 287.262 ሄ/ር (15.49%)፣ ከትራንስፖርት 1887.96 ሄ/ር ውስጥ 488.11 ሄ/ር (26.33%)፣ ከመዝናኛ እና ያልለሙ አከባቢ ከ3108.795 ሄ/ር ውስጥ 39.70 ሄ/ር (2.14%) የለማ ሲሆን በአጠቃላይ ከ15,733.00 ሄ/ር ውስጥ ነባሩ ተቀናሽ ተደርጎ ሲሰላ 1853.919 ሄ/ር መልማት ተከናውኗል።

በከተማችን በለፉት ዓመታት በተለዩ ሰፈሮች 2,668 ህገወጥ ግንባታዎች ተገንብተው 1,088 የሚሆኑትን በተደረጃ መልኩ በመፍረስ እና ህገዊ እርምጀ ተወስዷል።
የመሬት መረጃ ስርዓትን ከደስተርን በተመለከተ
179
ሞንመንቶች
13,560
ህገዊ ይዞታዎች በመለያት
2,780
ይዞታ በመረጋገጥ
820
ይዞታዎችን የመመዝገብ ስራ
2013
የካዳስተር ስራ የተጀመረበት ዓመት

በከተማው 179 ሞንመንቶች ይገኛሉ። የካዳስተር የመሬት ምዝገበና መረጋገጥ ስራን በይፋ የተጀምረው ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን 13,560 ህገዊ ይዞታዎች በመለያት፣ 2,780 ይዞታ በመረጋገጥ፣ 820 ይዞታዎችን የመመዝገብ ስራ ተሰርቷል።

የመሰረተ ልማት ስራዎች

እስከ 2014 ዓ/ም ድረስ 109,000,000 ብር፣ በ2015 በጀት ዓመት ደግሞ 40,887,993.3 ብር በድምሩ 149,887,993.3 ብር፣ 74,000,000 ከአከባቢ የተዛማጅ መዋጮ በድምሩ 223 ሚሊዮን ብር በላይ መድበን በስራ ላይ አውለናል።

13.2 ኪ.ሜ
የኮብልስቶን መንገድ
22.3 ኪ.ሜ
የጎርፍ መውረጃ ቦይ/ዲች
24
ከልቨርቶች እና 1 ድልድይ
122+
ሼዶች እና ኮንቴነሮች
2 ኪ.ሜ
የአረንጓዴ ልማት ማስዋብያ
15+ ኪ.ሜ
የውሃ መስመር ዝርጋታ

በቁጥር 8 እና 4.3 ሄክታር መናፈሻዎች እና 5.2 ሄክታር የህዝብ ፓርክ ለምቶዋል።

13. ኢንቨስትመንት መረጃ

የተላለፈ የኢንቨስትመንት መጠን (በሄክታር)
ዘርፍየተላለፈ መሬት (ሄ/ር)
አገልግሎት34
ከተማ ግብርና9
ኢንዱስትሪ176
ሪል ስቴት21
ሆቴል31
ሎጅ3
ንግድ52
በለፉት ዓመታት የንግድና መኖሪያ የቀረባ ፕሎት ብዛት (2012-2015)
ተ.ቁ ዓ.ም መኖሪያ የቀረበ ዙር የቀረባ ፕሎት ብዛት ንግድ የቀረበ ዙር የቀረበ ፕሎት ብዛት
12012-201511 ዙር1,1958 ዙር261
የተላለፈ መሬት በዘርፍ እና በዓመት (2011-2015)
ዓመት ኢንዱስትሪ መኖሪያ ኢንቨስት ሪል ስቴት ለንግድ
201115.77.35.280.52.12
201223.7118.535.28
201325.0515.9611910.54
201424.518.310.541115.7
201528.5418.915.71519.2
የጨረታ መረጃ - መኖሪያ
ተ/ቁ የከተማው ስም የቦታው አገልግሎት የጨረታ ቁጥር አማካይ ተሳታፊዎች ከፍተኛ አሸናፊ ዋጋ (ብር) ዝቅተኛ አሸናፊ ዋጋ (ብር)
1ወራቤመኖሪያ1454,400500
2ወራመኖሪያ1633,794125
3ወራቤመኖሪያ1732,513600
4ወራቤመኖሪያ1885,278505
5ወራቤመኖሪያ19137,529540
6ወቤመኖሪያ2032,5001,551
7ወራቤመኖሪያ2164,5321,405
8ወራቤመኖሪያ2296,5002,100
9ወራቤመኖሪያ23127,2502,910
10ወራቤመኖሪያ24167,8503,720
11ወራቤመኖሪያ25147,7284,160
የጨረታ መረጃ - ንግድ
ተ/ቁ የከተማው ስም የቦታው አገልግሎት የጨረታ ቁጥር አማካይ ተሳታፊዎች ከፍተኛ አሸናፊ ዋጋ (ብር) ዝቅተኛ አሸናፊ ዋጋ (ብር)
12ወራቤንግድ21910,5051,012
13ወራቤንግድ2278,8555,000
14ወራቤንግድ23810,500715
15ወራቤንግድ24810,5051,012
16ወራቤንግድ2578,7003,059
17ወቤንግድ2678,8555,000
18ወራቤንግድ2757,6784,305
19ወራንግድ2836,5023,610

14. የወራቤ ከተማ የነጋዴ መረጃ

በወራቤ ከተማ የነጋዴዎች ብዛት ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።

የነጋዴዎች እድገት በደረጃ (2011-2015) / Merchants Growth by Grade
የነጋዴ መረጃ በደረጃ (2011-2015)
ዓመት ደረጃ ሀ ደረጃ ለ ደረጃ ሐ ድምር
2011182789931,253
2012197841,1561,437
2013211971,3061,614
2014231941,6451,970
2015256991,9942,349
ማጠቃለያ፡ በአምስት ዓመታት ውስጥ የነጋዴዎች ብዛት ከ1,253 ወደ 2,349 በ87.5% አድጓል። የደረጃ ሐ ነጋዴዎች ቁጥር ከ993 ወደ 1,994 በ100.8% አድጓል።

ወራቤ ከተማ አስተዳደር

የማህበራዊ-ኢኮኖሚ እና ጂኦ-ስፓሻል መረጃ ትንተና

© 2017 ዓ.ም | ሶፍትዌር ገንቢ፡ አብዱልሀፊዝ ሰራጅ

Software Developer: Abdulhafize Seraje